Loading......
template-img

በተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

1.የተጋቢዎች ፈቃድ ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነጻና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሊሰጡ ይገባል። ጋብቻ የቤተዘመድ ጉዳይ ሳይሆን በቀዳሚነትና በዋናነት የተጋቢዎቹ ጉዳይ ነው። 2.የተጋቢዎች እድሜ ለወንዱም ሆነ ለሴቲቱ ዝቅተኛው የጋብቻ እድሜ 18 ዓመት ነው። ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት የፍትህ ሚኒስትሩ ከመደበኛው የጋብቻ እድሜ ከ2 ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል። 3.ዝምድና በተጋቢዎች መካከል የሥጋም ሆነ የጋብቻ ዝምድና ሊኖር አይገባም። በቀጥታ የሥጋ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ሲሆን ወደ ጎን በሚቆጠር የሥጋ ዝምድና አንድ ወንድ ከእህቱ ወይም ከአክስቱ እንዲሁም አንዲት ሴት ከወንድሟ ወይም ከአጎቷ ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነው። የጋብቻ ዝምድናን በተመለከተ ደግሞ፣ በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈጸም የተከለከለ ሲሆን ወደ ጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዝምድና ባል ከሚስቱ እህት ወይም ሚስት ከባሏ ወንድም ጋር ጋብቻ መፈጸም ክልክል ነው። 4.በጋብቻ ላይ ጋብቻ ሊሆን የማይገባ ስለመሆኑ ማንኛውም ሰው አስቀድሞ በጋብቻ የተሳሰረ ከሆነ ይኸው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ መፈጸም አይችልም። 5.በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ ሊጠበቅ የሚገባ መሆኑ አንዲት ሴት የፊተኛው ጋብቻዋ በባሏ መሞት ወይም በፍቺ ወይም በሌላ ሕጋዊ ምክንያት አብቅቶ ሌላ ጋብቻ ከመፈጸሟ በፊት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ 180 ቀናት መጠበቅ ይኖርባታል። አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ 180 ቀናት ካላለፈ በስተቀር እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችል

ይህ ክልከላ ሴቲቱ ምናልባት ከፊተኛው ትዳር ጽንስ ይዛ ወጥታ እንዳይሆንና ይህ ጽንስ በሁለተኛው ትዳር ውስጥ ከተወለደ በልጁ አባት ማንነት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የአባትነት ግጭት ለማስወገድ የተቀመጠ እንደሆነ ይታመናል። ዳሩ ግን፣ ሴቲቱ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ 180 ቀን ባይሞላትም የወለደች እንደሆነ፣ ወይም ጋብቻውን የምትፈጽመው ከቀድሞ ባሏ ጋር የሆነ እንደሆነ፣ ወይም እርጉዝ አለመሆኗ በሕክምና የተረጋገጠ እንደሆነ፣ ወይም በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነውን ጊዜ እንዳትጠብቅ ፍርድ ቤት የወሰነ እንደሆነ በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነውን ጊዜ መጠበቅ ሳያስፈልጋት ጋብቻውን መፈጸም ትችላለች።

Previous Post Next Post

(0) comments to this article

No Reviews

Leave a reply